ዓለምአቀፋዊ የሰዎች ኃላፊነት መግለጫ
ለውጥ
ግብን ለለውጥ እና ለእንክብካቤ መዘጋጀት

የኑሮ ዋስትናን መጨመርና እና መከራን መቀነስ
-
በቡድን ሰለምንወስደው እርምጃችን ውጤቱን መረዳት
-
የአኗኗር ስርዓትን እና በወስጡ የሚገኙትን ሁሉ ህይዎቶችን ከጥፋት መከላከል
-
ወሳኝ የሆኑትን የተፈጥሮ እና የባህል ቅርሶቻችንን ተንከባክቦ ማቆየት
-
ብክለትን መቀነስ እና የምድርን ስርዓት ሚዛናዊነት መጠበቅ
-
ችግርን ለማስወገድ የሚያስችል ሃብት ካለ ማንም ከችግር ነጻ መሆኑን ለማረጋገጥ መስራት
-
ስኬትን በጥሩ መመዘኛ እና በተጨባጭ መረጃ መተርጎም
-
ለእድገት/ለመለወጥ ወይም ላለመለውጥ ተጠያቂ እና ግልጽ መሆን

ምርጫ
ነጻነትን ማክበር እና የውስንነትን ጣሪያ እንደየ አሰተሳሰቡ ዋጋ መሠረት ማሰተዳደር
መረጃ ያለው ዜጋ መሆን እና ምርጫን በእውቀት ላይ ተመስርቶ ማድረግ
-
ነውጠኝነትን ማስወገድ እና ቅራኔን በሰላም መፍታት
-
ስለ ኑሮአችን እና ስራችን እውቀት እና ሁሉን አቀፍ አማራጮችን መጠቀም
-
በየእለቱ ሰለምንወስዳቸው ምርጫዎች ጥቅም እና ጉዳትን መረዳት
-
ለመሬት ደህንነት እና ቀጣይነት የሚጠቅም ኑሮን መኖር
-
ስለመሬት እና ሰዎች ታሪክ መማር
-
ስለ ሌሎች ህዝቦች፣ ህብረተሰቦች እና ስለ ማህበረሰባችን መማር
-
የማህበረሰብንና የግልን ጥቅሞችን ማስታረቅ

ችሎታ
ጠቃሚ የሆኑትን ችሎታን መፍጠር፤ ጎጂ የሆኑትን መቀነስ።
ዓላማዎችን በጥራት እና በብቃት ለማሳካት የሚያስችል ዘዴ መፍጠር
-
ለእያንዳንዱ ህጻን ጥራት ያለው ትምህርት መስጠት እና መልካም ጤንነትን መደገፍ
-
ለመኖር የሚበቃ ደሞዝ ሊያሰገኝ የሚችል የተሟላ የሙያ አማራጭን መፍጠር
-
የሚጠበቅብንን ማህበራዊ ግዴታዎቻችንን መወጣት እና መብታችንን ማስጠበቅ
-
ውስን ሃብቶችን በጥንቃቄ እና ያለብክነት መጠቀም
-
ዓላማችንን ለማሳካት የሚያስችሉትን የፈጠራና አመቺ ቦታን ሁኔታንማዘጋጀት
-
ጉዳት ሊያመጡ የሚችሉ እና የጋራ ዓላማን ሊያቀጭጩ የሚችሉ ስርዓቶችን ማፍረስ
-
የጋራ ንብረቶችን፣ አገልግሎቶችን፣ Aቅምን ያገናዘበ ኃይልን፣ መሠረተ ልማቶችን ማሳደግ
ማህበረሰብ
ዓለማቀፋዊ አንድነትንና ከነ ልዩነቶቻችን መፍጠር

ለራሳችን መጠንቀቅ Eና Eርስ በርሳችን መረዳዳት
-
ራስን በመከላከል ዘዴ ራሳችኝ ከጉዳት መጠበቅ
-
የራስን እንክብካቤ፣ የአካል ብቃት፣ የአካል እና የአእምሮ ጤንነትን ግንዛቤ ማሳደግ
-
ራሳቸውን መንከባከብ ለማይችሉ ወይም ለተገለሉ ሰዎች እንክብካቤ ማድረግ
-
ድህነትን፣ ረሃብን፣ ጭቆናን እና ተስፋብስነትን ለማስወገድ መስራት
-
ከእኛ ልዩ የሆኑ ሰዎችን ማክበር እና ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ
-
የጾታ እኩልነትን ማሳደግ እና ሌሎች ልዩነቶችን ማስወገድ
-
የጋራ ትብብርን መፈለግ እና በጋራ ደንቦች መሠረት መወዳደር